የደብረ ነጓድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የፍቁረ እግዚእ ሰ/ት/ቤት የ ዓመት የአገልግሎት ጉዞ::
የሰንበት ትምህርት ቤቱ አመሠራረት
የፍቁረ እግዚእ ሰ/ትቤት የተመሠረተው በ1950ዎቹ መጨረሻ አካባቢነው አስቀድሞ አመሠራረቱ በወጣቶች ማህበርነት ሲሆን በወቅቱ በነበሩት የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በመጋቤ ካህናት ዘውዴ አማካኝነት ቅርጽ ባለው ሁኔታ ሰንበት ትምህርት ቤቱ እንዲቆቆም ተደርጎ የመጀመሪያ ዓመት የምሥረታ በዓሉን በ1960 ዓ.ም በአዲስ ከተማ ት/ቤት አክብሯል በወቅቱ ትምህርቱ እና አገልግሎቱ የሚሰጠው ባሳምንት ሁለት ቀን የነበረ ሲሆን ቅዳሜ ከሰዓት የቅዳሴ ተስጥኦ እና ያሬዳዊ ዝማሬ እሁድ ጠዋት ደግሞ ሰፊ የትምህርተ ወንጌል አገልግሎት ይሰጥ ነበር፡፡ ሰ/ትቤቱ ከተመሠረተበት ጊዜ ጅምሮ አገልግሎቱን እያሰፋ የመጣ ሲሆን ያለፋትን ዓመታት የቤተክርስቲያን ተልዕኮ ይሳካ ዘንድ የአካባቢውን ወጣቶች በማስተባበር ሰፊ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶል እየሰጠም ይገኛል፡፡ በተለይ በስብከተ ወንጌል አገልግሎት በኩል በአጥቢያው ያሉ ምዕመናንን በመሰብስብ በዓወደ ምህረት የሰርክ ጉባኤን በመጀመር ማስተማሩ ለብዙ የአዲስ አባባ አድባራት እና ገዳማት አርአያ ያሆነ አገልግሎት ሆኖል ወጣቶችን እና ሕጻናትን በመሰብሰብ ተከታታይ የሃይማኖት ትምህርትን በማስተማር በሃይማኖት እና በምግባር ተኮትኩተው እንዲያድጉ አድርጎል፡፡
እነሆ ዛሬ ሰ/ትቤታችን ከተመሠረተች ዓመት ሞላት በእነዚህ ዓመታትም ውስጥ ለቤተክርስቲያን ብሎም ለሀገር ያበረከተቻቸው ተግባራዊ አበርክቶዎች ከብዙ በጥቂቱ፡-
የሰንበት ትምህርት ቤቱ ዓላማ
1. ዓላማ አንደኛ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት እና ሥርአት ተጠብቆ ሳይለወጥ ሳይበረዝ በቀጥታ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ
2. ዓላማ ሁለተኛ
ማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ አባል የሆነ ክርስቲያን ሁሉ ሃይማኖቱን እና የሃይማኖቱን ሥርዓት በውል እንዲያውቅ እንዲረዳ ማድረግ
3. ዓላማ ሶስተኛ
መንፈሳዊያን ወጣቶች በሰንበት ትምህርት ቤት ተሰብሰበው እየተማሩ የሀገርንም ሆነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በሚገባ አውቀው በሃይማኖት ትምህርት እና በሥነ ምግባር ብስለት እንዲያገኙና የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ለመረከብ ብቁዎች እንዲሆኑ ማድረግ
4. ዓላማ አራተኛ
ወጣቶች የቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ቃለ እግዚአብሔር ተምረው ወላጆቻቸውን ታላላቆቻቸውን አክባሪዎች እንዲሆኑ በአጠቃላይ በሃይማኖት በሥነ ምግባር ታንጸው እንዲያድጉ እና ለሀገርና እና ለወገን መልካም ዜጎች እንዲሆኑ ማድረግ
5. ዓላማ አምስተኛ
“ሽማግሌዎችን አትንቀፍ ነገር ግን ለእነርሱ እንደ አባት ለጎበዞችም እንደ ወንድሞችህ ታዘዝ ፡፡ ለባልቴቶችም እንደ እናትህ ታዘዝ ለወጣቶች ሴቶችም እንደ እኅቶችህ በፍጹም ንጽሕና ታዘዝ››
6. ዓላማ ስድስተኛ
“የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ” መጽሐፈ መክ ፲፪፥፩ ወጣቶች ለመንፈሳዊ አገልግሎት ጽኑዕ ፍላጎት እንዲያድርባቸው፣ የምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ተካፋይ እንዲሆኑ፣ በተሰማሩበት የሥራ መስክ አክብሮትና ታማኝነት እንዲኖራቸው ማስቻል፡፡
የሰንበት ትምህርት ቤቱ ራእይ
"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፣ ቀኖና እና ትውፊት አውቆ የሚያሳውቅ ጠብቆ የሚያስጠብቅ በመንፈሳዊ ሕይወቱ ጠንካራ የሆነ በመንፈሳዊ ትምህርትም በዘመናዊ ትምህርትም የበሰለ በሃይማኖት እና በምግባር የታነጸ ትውልድ ማየት"