በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደብረ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን.
መግቢያ
የአዲስ አበባ ደብረ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ከተማ በድሮ አጠራር ከፍተኛ 1 ቀበሌ 03 የሚገኝ ሲሆን አሁን በአራዳ ክፍለ ከተማ ከፒያሳ መናገሻ ገነተ ጽጌ (አራዳ) ቅዱስ ጊዮርጊስ ተነሥቶ በሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ ወደ አስኮ በተዘረጋው የአርበኞች መንገድ በራስ ደስታ ሆስፒታል አካባቢ ይገኛል ከመንበረ ፓትሪያሪክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የ3.6 ኪ ሜ ርቀት ያለው ሲሆን ስሙ ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ መባሉ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (የነጎድጓድ ልጅ) ተብሎ ስለሚጠራ ነው።
የቅዱስ ዮሐንስ ታቦት አመጣጥ
የፍቁረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ታቦት ከአፄ ዮሐንስ ዘንድ ነበረ። እርሳቸውም ለንጉሥ ሚካኤል ሰጡት። ታቦቱ አዲስ አበባ አራዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በደባልነት ገብቶ ተቀመጠ።
የነጋድራስ ሰርጸወልድ ቤት
ቤቱ በጊዜው ከነበሩት ቤቶች በአሰራሩ የተሻለ ሆኖ ፎቅና ምድር ያለው ሲሆን ታቦቱ ከሳር ክዳኑ ቤት ወጥቶ ወደዚህ ቤት በዚያው ዓመት በጥቅምት 4 ቀን 1914 ዓ.ም ቤቱ ተባርኮ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ በተገኙበት ለ2ኛ ጊዜ ታቦቱ እንዲገባ ተደረገ።
አሁን ያለው ሕንጻ ቤተክርስቲያን
እሱ ከመሠራቱ አስቀድሞ ልዑል መኮንን ኃይለሥላሴ እና ብላታ ተሰማ። በጊቢው ውስጥ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መቅደስ ያለ ሲሆን ብዙዎች በቅርብ ሆነ በሩቅ ያሉ ምእመናን ፈውስ እና በረከት ለማግኘት የሚጠመቁባቸው አሥራ አራት የተለያዩ ጠበሎች ያሉበት ቤተ ሳይዳ የተሰኘ የጠበል ቦታም ከቤተ ክርስቲያኑ አጠገብ ይገኛል።
የደብሩ አገልግሎት ክፍላት
የደብሩ አገልግሎት ክፍላት ለምእመናን መንፈሳዊ፣ ማህበራዊና አስተዳደራዊ ፍላጎቶች ሁሉ የሚመለስ ሰፊ አገልግሎት ይሰጣል።
- 1. የሰበካ ጉባኤ
- 2. ሰንበት ት/ቤት
የደብረ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን አለቃዎች
የደብረ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን አለቃዎች በተለያዩ ዘመናት ቤተ ክርስቲያኑን በእምነትና በጥበብ የመሩ ሲሆን፣ እስከ ዛሬ 24 አለቃዎች አገልግሎት አድርገዋል።
- 1. መምህር ኮከብ
- 2. መምሬ ዘውዴ
- 3. መምህር ሰሎሞን
- 4. መጋቤ ካህናት ዘውዴ ወ/ማርያም
- 5. መምህር ብርሃነ ሥላሴ
- 6. መምህር መዘምር ተገኝ
- 7. መምህር ኪዳነማርያም አለባቸው
- 8. መምህር ተወልደመድኅን ወ/ጊዮርጊስ
- 9. መልአከ ብርሃናት አደራው ንጉሤ
- 10. መልአከ ኀይል ወልደ ያሬድ መኩሪያ
- 11. መልአከ አርያም ዘለዓለም እሰይ
- 12. መምህር አባ ኀይለ ማርያም ስጠኝ
- 13. መልአከ አርያም ሐረገ ወይን ብርሃኑ
- 14. መጋቤ ሐዲስ አባ መልካሙ
- 15. መልአከ አርያም አወቀ ተሰማ
- 16. መልአከ አርያም አደራው
- 17. ሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ማርቆስ
- 18. ቆሞስ አባ ሀይለ ሚካኤል
- 19. መልአከ ገነት ክብሩ ገ/ፃድቅ
- 20. መልአከ ብርሃናት ዘመንፈስ ቅዱስ ገ/አምላክ
- 21. መልአከ ሰላም ሰሎሞን ተካ
- 22. መልአከ አሚን አባ ኃይለመለኮት ይሄይስ
- 23. መልአከ መንክራት ሀይሌ አብርሃ
- 24. መልአከ ገነት መዝገቡ ላቀው
ቤተሳይዳ (ጠበል ቤት)
የጠበል ቤቱ ከቤተ ክርስቲያኑ በስተደቡብ ይገኛል፣ 2,100 m2 የሚሸፍን ሲሆን በግቢው ውስጥ ብዙ ጠበሎች አሉ።
- 1. የሥላሴ ጠበል
- 2. የእግዚአብሔር አብ ጠበል
- 3. የመድኀኔ ዓለም ጠበል
- 4. የአማኑኤል ጠበል
- 5. የእመቤታችን የማርያም ጠበል
- 6. የኪዳነ ምሕረት ጠበል
- 7. የቅዱስ ዮሐንስ ጠበል
- 8. የቅዱስ ሚካኤል ጠበል
- 9. የቅዱስ ገብርኤል ጠበል
- 10. የቅዱስ ሩፋኤል ጠበል
- 11. የቅዱስ ጊዮርጊስ ጠበል
- 12. የአቡነ ተክለሃይማኖት ቅዱስ ጠበል
- 13. የአቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ጠበል
- 14. የአቡነ አረጋዊ ቅዱስ ጠበል