ቅዱስ ዮሐንስ አቡቀለምሲስ (ወልደ ነጎድጓድ)

ሐዋርያው፣ ወንጌላዊውና ፍቁረ እግዚእ

ልደቱና ጥሪው

ሐዋርያው ዮሐንስ ከዘብድዮስና ከማርያም ባውፍልያ መስከረም አራት ቀን ተወልዶ። በገሊላ አካባቢ አድጎ ገና በወጣትነቱ መድኃኒአለምን ተከትሎታል። ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጎኑ አይጠፋም ነበር። ስለንጽሕናውና በጎ የፍቅር ሕሊናው ሕፃን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው። ዮሐንስ የሚለው ስም ዮሐናን ከሚለው ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም “ከያሕዌ (ከእግዚአብሔር )የተሰጠ“ ማለት እንደሆነ ብዙ ሊቃውንት ይስማማሉ። ትርጓሜ ወንጌል ግን “ዮሐንስ ማለት ፍስሐ ወሐሴት ማለት ነው" ይላል::


የቅዱስ ዮሐንስ ቅጽል ስሞችና ትርጉማቸው

ቦኤኔርጌስ

የነጎድጓድ ልጅ (ወልደ ነጎድጓድ)

ታኦሎጎስ

ነባቤ መለኮት (ስለ መለኮት የሚናገር)

አቡቀለምሲስ

ባለ ራዕይ (ረአየ ኅቡአት)

የተለዩ ባህርያቱ

  • 🛡️ ቁጹረ ገጽ፡ የጌታን መከራ በማሰብ ፊቱ በሐዘን የተቋጠረ።
  • 🦅 ዘንስር፡ ከደመና በላይ እንደሚበር ንስር ረቂቅ ምስጢራትን የመረመረ።
  • 🤱 የአደራ ልጅ፡ እመቤታችንን በጌታ አደራ ተቀብሎ ለ16 ዓመታት ያገለገለ።
  • 🤍 ድንግል፡ በንጽሕናውና በፍቅሩ በጌታ ደረት ይደገፍ የነበረ።

ስብከተ ወንጌልና ተአምራት

ቅዱስ ዮሐንስ በአንጾኪያ፣ በሎዶቅያና በኤፌሶን በስፋት አስተምሯል። በኤፌሶን በነበረበት ወቅት ሮምና በምትባል ሴት ቤት በእንጨት ፈላጭነት ሲያገለግል የሞተ ልጅን በማስነሳት ተአምር አድርጓል።

"በፍጥሞ ደሴት ተግዞ ሳለ ታላቁን የዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ ጽፏል።"
የበዓሉ ቀን የበዓሉ ምክንያት
መስከረም 4 የልደቱ መታሰቢያ በዓል
ግንቦት 16 ራዕይ ያየበት (ፍጥሞ ደሴት)
ጥር 4 ታላቁ የስውረት (ዕረፍት) በዓል

"ሞትን ሳይቀምስ እንደ ሄኖክና እንደ ኤልያስ የተሰወረ ቅዱስ ነው።"
የቅዱስ ዮሐንስ ረድኤት በረከት አይለየን!