July 03, 2026 ዜና (News)
  • 18
  • ለደብሩ ማሕበረ ካህናት በልዩ ልዩ ርዕሰ  ጉዳዮች ላይ ሥልጠና ተሰጠ።

    ለደብሩ ማሕበረ ካህናት በልዩ ልዩ ርዕሰ  ጉዳዮች ላይ ሥልጠና ተሰጠ።

    በደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎለጎታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከሰኔ 24 -26 /2018 ዓ.ም ለሦስት ቀናት  የቆየ  ለካህናት፣ ለዲያቆናት እና ለደብሩ ልዩ ልዩ አገልጋዮች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ተሰጥቷል ።

    ስልጠናው  ትምህርተ ኖሎት፣  ዕቅበተ እምነት እና ተልኳችን በሚሉ  ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ  በተለያዪ የቤተክርስቲያናችን መምህራን  የተሰጠ ሲሆን የአዲስ አበባና የሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣  ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በስልጠናው  ተገኝተው በተዘጋጀው  ስልጠና ተደስተው  ለቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እንደዚ አይነት የተለያዩ ስልጠናዎችን መሰጠት ያለውን ጠቀሜታ አንስተው ካህናት ከምእመናን እና ከንስሐ ልጆቻቸው ጋር  ዘመኑ በዋጀ መልኩ አገልግሎታቸውን እንዲፈጽሙ ቤተ ክርስቲያናቸውን  በጥልቀት እንዲያውቁ እና የመፍትሔ አካል እንዲሆኑ   እንዲህ አይነት ስልጠዎች በቋሚነት መስጠት እንደሚገባ መመሪያ ሰጥተዋል ።

    በስልጠናው የተሳተፉ  የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮች በስልጠናው እንደተደሰቱ ከንሰሐ ልጆቻችን ጋር  ያለን ግንኙነት እንዴት መሆን እንዳለበት  ዘመኑን በዋጀ መልኩ የተረዳንበት ነው ብለዋል ።  በቀጣይነት እንደዚ አይነት መሰል ስልጠናዎች ቢሰጡ መሻታቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

    በስልጠናው ላይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ለይኩን አበጀ የተገኙ ሲሆን በመጨረሻም ለስልጠናው ተሳታፊዎች እና ለስልጠናው መሳካት ድጋፍ ላደረጉ አካላት ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የተዘጋጀውን የምስክር ወረቀት አበርክተውላቸዋል።