September 07, 2026 ዜና (News)
  • 7
  • የዓመቱን የመጨረሻ የደም ልገሳ መርሐ ግብር ተካሄደ።

    የዓመቱን የመጨረሻ የደም ልገሳ መርሐ ግብር ተካሄደ።

    በደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና መካነ ጎለጎታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን  የፍቁረ እግዚእ ሰ/ት/ቤት ከኢትዮጵያ ደምና ሕብረ ሕዋስ ባንክ አገልግሎት ጋር በመተባበር የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናወነ።

    በተዘጋጀው የደም መለገስ  መርሐ ግብር ላይ የደብሩ አገልጋዮች ፣ የሰንበት ት/ቤቱ አባላት እና ምዕመናንን በአጠቃላይ ከ182 በላይ ሰዎች ደማቸውን እንዲለግሱ የተደረገ ሲሆን በዚህም ከ546 በለይ በደም እጦት በሞትና በህይወት መካከል ለሚገኙ ወገኖችን  የተለገሰው ደም ሕይወት ማትረፍ እንደሚያስችል የጤና ባለሙያዎች ገልጸዋል ።

    የደብሩ ማሕበረ ካህናት ፣ የሰንበት ት/ቤቱ አባላት እና ምእመናን በተለያየ ምክንያት ደም ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች  ደም በመለገስ ሕይወታቸውን ከሞት ለመታደግ ለምታደርጉት አስተዋጾ  ሰ/ት/ቤቱ ምስጋና  ያቀርባል።

    ደም በመለገስ የወገኖቻችን ሕይወት እንታደግ‼