September 06, 2026 ዜና (News)
  • 8
  • የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት በተለያዩ የትምህርት መስኮች  ያስተማራቸውን ከ800 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።

    የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት በተለያዩ የትምህርት መስኮች  ያስተማራቸውን ከ800 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።

    በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አንጋፋ ከሚባሉት  ሰንበት ት/ቤቶች አንዱ የሆነው የደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና መካነ ጎለጎታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም በተለያዩ የትምህርት መስኮች  ያስተማራቸውን ተማሪዎችን በዛሬ ዕለት  አስመርቋል።

    በአምስት የትምህርት መስክ ማለትም በተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት ፣ በበገና የዜማ መሣሪያ ፣ በኦርቶዶክሳዊ ቅደሣት ሥዕላት አሳሳል፣ በሞካሽ ሥራ እና በሥነ ጽሑፍ አጻጻፍና ትወና ትምህርታቸውን ተከታትለው  ያጠናቀቁ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት የተመረቁ ሲሆን በምርቃት መርሐ ግብሩላይ የደብሩ ዋና አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ለይኩን አበጀ  የደብሩ ሰበካ ጉባኤ አባላት  የሰንበት ትምህርት ቤቱ አገልጋይ አባላት እና የተመራቂ ተማሪዎች ቤተሰቦች ተገኝተዋል ።

    በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ በተመራቂ ተማሪዎች ልዩ ልዩ የበገና ዝማሬዎችን እና የቸብቸቦ ዝማሬዎች ፣ በመዘምራን ወረብ የቀረቡ ሲሆን ትምህርታቸው ላጠናቀቁ ተማሪዎች  የአደራ መስቀል እና የላቀ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ደግሞ የማበረታቻ ሽልማት በደብሩ ዋና አስተዳዳሪ እና በዕለቱ የክብር እንግዳ ተበርክቶላቸውል።

    በመጨረሻም የደብሩ ዋና አስተዳዳሪ  ባስተላለፉት መልእክት ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት በተማራችሁት ትምህርት ጸንታችሁ  ለቀጣዩ ትውልድ የተማራችሁትን በማስተማር ለተተኪ ትውልድን ለማፍራት ትኩረት ሰጥታችሁ  እንድትሰሩ በማለት  ተመራቂ ተማሪዎች በሙያቸው ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲያገለግሉ አሳስበው  መርሐ ግብሩ በቃለ ምዕዳን እና  ቡራኬ ተጠናቋል ::