September 06, 2026
ዜና (News)
7
የ2018ዓ.ም የሰንበት ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የምረቃ መርሐ ግብር ተከናወነ።
የ2018ዓ.ም የሰንበት ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የምረቃ መርሐ ግብር ተከናወነ።
በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በሥርዓተ ትምህርቱ በቅድመ ትግበራ ሙከራ ሲከናወንባቸው ለነበሩ እና ለዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን በዛሬው ቀን አስመረቀ።
ለምርቃት የደረሱት ተማሪዎች ከሁለት ሀገረ ስብከት የተውጣጡ የ19ሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሲሆኑ በምርቃት መርሐ ግብሩ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ ሐላፊ መጋቤ ሐዲስ ኀይለ እግዚ አሰፋ፣ የማደራጃ መምርያው ትምህርት ክፍል ሐላፊ መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ይታገሱ ደሴ የሀገር አቀፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ተቀዳሚ ምክትል ሰብሳቢ ዲያቆን ዶክተር ስንታየሁ ምስጋናው በመገኘት ለተማሪዎች መልዕክት አሰሰተላልፈዋል።
በመርሐ ግብሩ ለተማሪዎች የሰርተፍኬት እና በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማት እና በትምህርት ትግበራ እግቅስቃሴ የላቀ ውጤት ላስመዘገበው ደብር የማበረታቻ ሽልማት በመስጠት የመርሀግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
© ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት