July 27, 2026 ዜና (News)
  • 1
  • በደብረ ታቦር ደብረ ልዑላን መድኃኔዓለም የ4ቱ ጉባኤ ምስክር ጉባኤ ቤት በአቡነ መልከ ጼዴቅ ስም የተሰየመ ቤተ መጻሕፍት ተመረቀ።

    በደብረ ታቦር ደብረ ልዑላን መድኃኔዓለም የ4ቱ ጉባኤ ምስክር ጉባኤ ቤት በአቡነ መልከ ጼዴቅ ስም የተሰየመ ቤተ መጻሕፍት ተመረቀ።

    በደብረ ታቦር ደብረ ልዑላን መድኃኔ ዓለም የ4ቱ ጉባኤ ምስክር ጉባኤ ቤት በአቡነ መልከ ጼዴቅ ስም የተሰየመው ቤተ መጻሕፍት ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ተመርቋል።

    በዚሁ የምርቃት መርሃ ግብር ላይ የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት እና የደብረ ታቦር ወረዳ ቤተ ክህነት የሥራ አመራሮች፣ ከተለያዩ መሥሪያ ቤቶች የተወጣጡ ተወካዮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ እናቶች እንዲሁም በርካታ ሕዝበ ክርስቲያን ተገኝተውበታል።

    የጉባኤ ቤቱ መምህር መምህረ መምህራን በጽሐ አለሙ በምርቃቱ ወቅት ባስተላለፉት መልእክት፤ የቤተ መጻሕፍቱ መከፈት የትምህርት ማዕከሉን አቅም እንደሚያሳድግ ገልጸው፣ የመጻሕፍት ክምችቱን ለማበልጸግ የሁሉም ምእመናንና ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። ይህን ቤተ መጻሕፍት ስናስመርቅ ሙሉ በሙሉ የተሟሉ መጻሕፍትን ይዘን ሳይሆን፣ የመጻሕፍት ማስቀመጫዎቹን ስለሠራን ነው። ስለዚህ እናንተ የምትችሉትን በመግዛት፣ እንዲሁም አንብባችሁ ያስቀመጣችኋቸውን ማንኛውንም ዓይነት መጻሕፍት ለቤተ መጻሕፍቱ በስጦታ ብታበረክቱልን እኛ ለመንፈሳዊ ዕውቀትና ምርምር እንጠቀምባቸዋለን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። አያይዘውም ከ12 ሺህ በላይ መጻሕፍትን በማሰባሰብ የጥንታውያኑን አባቶች ታሪክና ዕውቀት እንደገና መመለስ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

    በምርቃት መርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት መልካም ፈቃድ ለጉባኤ ቤቱ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት የኃላፊነት ስያሜ ተሰጥቷል። በዚህም መሠረት ከዚሁ ጉባኤ ቤት ተመርቀው ከወጡት መምህራን መካከል፦
    1, መምህር ፍሬ ስብሐት ካሳ — የጉባኤ ቤቱ የሐዲስ ኪዳን መምህር፤
    2, መምህር ቃለ ሕይወት ይመኑ — የጉባኤ ቤቱ ምክትል መምህር አድርጎ
    በመመደብ በተሰጣቸው ምደባ መሠረት፣ ያከበቱትን ጥልቅ ዕውቀት ለተተኪው ትውልድ የማስተላለፍ አደራ ተረክበዋል።

    © በደብረ ታቦር ደብረ ልዑላን መድኃኔዓለም የ4ቱ ጉባኤ ሚዲያ
    ❤2