ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በኢትዮጵያ የታላቋ ብሪታንያ አምባሳደር እና በአፍሪካ ኅብረት የቋሚ መልእክተኛ ክቡር ዳረን ዌልችን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በኢትዮጵያ የታላቋ ብሪታንያ አምባሳደር እና በአፍሪካ ኅብረት የቋሚ መልእክተኛ ክቡር ዳረን ዌልችን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤ በኢትዮጵያ የታላቋ ብሪታንያ አምባሳደር እና በአፍሪካ ኅብረት የቋሚ መልእክተኛ ክቡር ዳረን ዌልችን (HE Darren Welch | UK Ambassador to Ethiopia & Permanent Representative to the African Union) በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
አምባሳደር ዳረን ዌልች ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ያደረጉትን ውይይት አስመልክተው ለኢኦተቤ ቴቪ በሰጡት አስተያየት፤ በኢትዮጵያ እና በእንግሊዝ መካከል ከጥንት ጀምሮ፣ በኋላም ዘመናዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ከተመሠረተበት ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት አንስቶ ለዘመናት የዘለቀ ጠንካራ ታሪክ እንዳለ አስታውሰዋል።
አክለውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የበርካታ ጥንታዊ ታሪኮችና ቅርሶች ባለቤት፣ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ልዩ ገጽታና ትልቅ ቦታ ያላት የክርስቲያን መድረክ መሆኗን ገልጸዋል።
ቤተ ክርስቲያኗ ለሀገሪቱ ሰላም፣ ታሪክ እና ማህበረሰብ የምታበረክተውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያከብሩ የጠቀሱት አምባሳደሩ፤ ኢትዮጵያ የተለያዩ ሃይማኖቶች በሰላም አብረው የሚኖሩባት ድንቅ የህብረት አርአያ መሆኗን ጠቁመዋል ።
በመጨረሻም በኢትዮጵያ በተለያዩ ወቅቶች የሚስተዋሉ የሰላም እጦት እና የኢኮኖሚ አለመረጋጋቶችን ለመቅረፍ ከቤተ ክርስቲያኗ ጎን በመሆን ለጋራ ሰላም እና ለአብሮነት ተባብረው እንደሚሠሩ ገልፀዋል።
©eotc tv
🙏1