July 14, 2026
ዜና (News)
19
ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የሚኒሶታ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሮዝማውንት ሚኒሶታ የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ወቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ባጋጠመው የእሳት አደጋ
ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የሚኒሶታ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሮዝማውንት ሚኒሶታ የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ወቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ባጋጠመው የእሳት አደጋ
የተሰማቸውን ኃዘን ገለጹ።
በሚኒሶታ እና አካባቢው ሀገረ ስብከታችን ውስጥ ከሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት መካከል በROSEMOUNT, MINNESOTA በቅርብ ጊዜ ከ2.2 ሚሊዮን ዶላር በላይ የተገዛው እና በቅርቡ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሮ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ወቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ዛሬ ሐምሌ ፮ (Jul, 13) የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ወርሃዊ በዓል የቅዳሴ አገልግሎት ከተፈጸመ በኋላ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ በእሳት ተቃጥሏል፤
የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤልም የአደጋውን መከሰት እንደሰሙ በቦታው ተገኝተው በከፍተኛ ኃዘንና፣ ድንጋጤ ላይ የነበሩትን የደብሩን ካህናት፣ የሰበካ ጉባኤ አባላት፣ የሰ/ት/ቤት ወጣቶችና፣ ምዕመናንን በማጽናናትና አባታዊ ቡራኬ በመስጠት በቤተ ክርስቲያኑ በተከሰተው የእሳት አደጋ የተሰማቸውን ኃዘን ገልጸው በተከሰተው ችግር ዙሪያ ከደብሩ ካህናት ጋር ውይይት አድርገዋል።
"የቤተ ክርስቲያን አምላክ ከእንደዚህ ዓይነቱ ያልታሰበ አደጋ ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን!"
የሚኒሶታ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት
🙏5