July 13, 2026 ዜና (News)
  • 21
  • በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት 4ኛው የአህጉረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች መምህራን የአሠልጣኞች ሥልጠና በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ በዛሬው ዕለት ተጀመረ።

    በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት 4ኛው የአህጉረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች መምህራን የአሠልጣኞች ሥልጠና በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ በዛሬው ዕለት ተጀመረ።

    ሐምሌ 06/2018 ዓ.ም

    በዛሬው የመክፈቻ መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ አገልግሎት መምርያ ሊቀ ጳጳስ ፣ መጋቤ ሐዲስ ኃይለ እግዚእ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሐላፊ ፣ መጋቤ ሐዲስ ጸጋ ወልደ ትንሣኤ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት መምሪያ ሐላፊ ፣ ሊቀ ጉባኤ መሐሪ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ምክትል ሐላፊ ፣ ዲ/ን ስንታየሁ ምስጋና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ተቀዳሚ ምክትል ሰብሳቢ እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ሥራ አመራር አባላት እና የመምሪያው ልዩ ልዩ ሠራተኞች በተገኙበት በጸሎተ ወንጌል ተጀምሯል።

    ብፁዕ አቡነ ማርቆስ በመዝሙር 125(126):5 ላይ "በልቅሶ የሚዘሩ በደስታ ያጭዳሉ።" የሚለውን የዳዊት መዝሙር መነሻ አድርገው ገበሬ በልቅሶ በመከራ በክረምት ዘርን እንደሚዘራ በገበሬ አምሳል መምህራንም ዘር የተባለ ቅዱስ ወንጌልን በልቅሶ በመከራ ለማስተማር  መዘጋጀት ይገባችዋል በማለት ለሰልጣኝ መምህራኑ አባታዊ ቡራኬና መልእክት አስተላልፈዋል።

    "የተጠማ ቢኖር ወደኔ ይምጣና ይጠጣ በእኔ የሚያምን ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚል የሕይወት ውኃ ምንጭ ከሆዱ ይፈልቃል።" ዮሐ 7:38 በሚል ቃል መነሻ አድርገው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

    ❤2